
Hosted by — · ENGLISH

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ለ 90 ቀናት በተከታታይ በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የመረጃ እና ደህንነት ትምህርቶች ያሰለጠናቸውን ታጋዮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ አስመርቀ። ህዝባዊ ሃይሉ ከዚህ በፊት 4 ተከታታይ ዙሮችን ያስመረቀ ሲሆን የዛሬው ለአምስተኛ ጊዜ ነው። በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝባዊ ሃይሉ ዋና አዛዥ ኮማንደር አሰፋ ማሩ [&hellip

የወያኔን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሠራለን ቀን 19/12/2006 በአገራችን ኢትዮጵያ ላይ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ሥርዓት ለመቀየርና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ለማውረድ በተለያየ ጎራ ተከፍለው የሚታገሉ ድርጅቶች ቁጥር ከምንጊዜውም በላይ እየበረከተ መምጣቱ የጎጠኛውን ቡድን እድሜ በማራዘም ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱ አሌ የማይባል ሀቅ ነው። ወቅቱ የሚጠይቀውና አገራችንና ሕዝባችን ያሉበትን ደረጃ በአንክሮ የተረዳ አገርና ሕዝቡን አፍቃሪ የሆነ ድርጅትም ሆነ [&hellip

አዋጅ አዋጅ !!! ልብ ያለህ ልብ በል ጆሮ ያለህ ስማ !! የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በየመን መታገት አስመልክቶ አጭር መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል::በመግለጫችን የመን ታጋዩን ልታግት የምትችልበት የጸጉር ስንጣቂ የምታክል ምክንያት እንደሌላት ሊኖራትም እንደማይችል ስለሆነም ታጋዩ ባስቸኳይ እንዲለቀቅ በተደጋጋሚ ጠይቀን፣ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የነጻነት ታጋዩ ለፋሽስቱ የወያኔ ቡድን ተላልፎ ቢሰጥ

በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ከታዩ አርቆ አሳቢ፣ አስተዋይና ብልህ ፖለቲከኞች አንዱ የሆነው ታላቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሥራ ጉዳይ ሲንቀሳቀስ የመንን እንደመሸጋገሪያ በሚጠቀምበት ወቅት በሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በየመን ሰንዓ ከተማ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በሀገሪቱ መንግሥት ትዕዛዝ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል:: ምንም አይነት ምድራዊም ይሁን ሰማያዊ መነሻ ምክንያት [&hellip

የኢትዮጵያዊያንን ስቃይና መከራ ሊያቅብና እንባቸውን ሊየብስ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛው ሕወሃት የደረሰባትንና እየደረሰባት ያለውን ውርደት ወደ ክብር ለመለወጥና የናቋትና ያዋረዷት በፍትህ ሚዛን ላይ እንዲቀመጡና ፍርዳቸውን እንዲያገኙ ለማድረግ ዓላማየ ብሎ ምሎ ዱሩ ቤቴ ካለ ገና ሁለት ዓመት እንኳ ያልሞላው ግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል በቃሉ መሰረት አራተኛውን ዙር የታጋዮች የምረቃ በአል ሚያዚያ 26 2006 ዓ/ም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር [&hellip

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ ቀን ታህሳስ 7 2006 (PDF) (Audio mp3) ታህሳስ 7 2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት በጭንቅና በአሳር ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ፣ የአሳርና የውርደት [&hellip

ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራርአባላት ላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል ሙከራ ከሸፈ። በጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ሃይለማሪያም ደሳለኝ እውቅናና ትእዛዝ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች በሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሄድ አመራሩን ለመግደል ሙከራ ቢደረግም ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል ከፍተኛ ክትትል ሙከራው መክሸፉን ሕዝባዊ ሃይሉ ገለጸ። ይህ ልዩ ትእዛዝ ጥቅምት 30 2006 ዓ/ም ተፈጻሚ እንዲሆን እቅድ [&hellip

በኖርዌ የተደረገውን የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ግሩም ድንቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ጨምሮ ከሌላውም የዓለም ክፍል ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን ሕዝባዊ ሃይሉ ገለጸ። ይህንን ተከትሎም የአብረን እንታገል ጥሪ ከያቅጣጫው እየጎረፈለት መሆኑንም ጠቁሟል። ፋሽስት ወያኔ አንዴ በሊማሊሞ አቋርጡ ሌላ ጊዜ ደግሞ መንገዱን ጨርቅ የርግላችሁ ሲል እንደነበር ያስታወሰው ሕዝባዊ ሃይሉ ይኸው ያ ቀን ደርሷል ብሏል።

በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይልና በትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሃል መገንባት የጀመረውን ወገናዊ ትስስር የሚያሳይ የቪድዮና የዜማ ቅንብር

ከሃምሌ 26 _ 2005 አንስቶ ይህ መግለጫ እስከወጣበት እስከ ሃምሌ 28_ 2005 አ.ም እለት የወያኔ ዘረኛ ጉጅሌ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮቹን በማሰማራት በመላው ኢትዮጵያ፣ በእስልምና እምነት ተከታይ የሃገሪቱ ዜጎች ላይ በስፋት የግድያ እርምጃ እየወሰደ ነው። ክቡር ህይወታቸውን በግፈኛው የወያኔ የአፈና ሃይል ያጡት ወገኖች ቁጥር በርካታ ሆኗል። ክፉኛ የቆሰሉት ወገኖቻችን ቁጥር ከተገደሉት እጅጉን የገዘፈ ነው። ፍጹም አረመኔያዊነት በተሞላው መንገድ በወያኔ ቅልብ ጦር የተቀጠቀጡትና እንደከብት ተሰብሰብው በየእስር ቤቱ የታጎሩት ወገኖቻችን ቁጥር በሽዎች የሚቆጠር ሆኗል።