
Hosted by ዐቢይ ሀብታሙ · EN

''እንደኔ አሜሪካ በኢራንና በሶማሊያዊው ዳኛ ላይ የያዘችው አቋም የፖለቲካ አቋም ነው። ለነዚህ ሀገራት ያላት አመለካከት ምን ይመስላል የሚለውን ነገር ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል —ፊፋ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ድጋሚ እንዲፈጠሩ መፍቀድ የለበትም '' ሲል አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ ከሰሞኑ በካናዳ፣ ሜክሲኮና አሜሪካ አማካኝነት እየተሠናዳ የሚገኘው የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውዝግቦችን ከሜዳና ውስጥና ሜዳ ውጪ ክስተቶች ጋር በማጣመር እንወያያለን። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱና ሌላኛው የስፖርት ጋዜጠኛ ሳምሶን አበበ ሙያዊ ዕይታቸውን አጋርተውናል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

''የሳተላይት መረጃ በመሠረታዊነት ነገሮች ከመባባሳቸው በፊት ቅድመ እና ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል። ለምሳሌ የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የሰብል ውድቀትን አስቀድሞ ለመተንበይ ወይም ለመገመት እንችላለን ምክንያቱም ከሳተላይቶች፣ በጣም ትንሽ የሆነ የእርሻ ቦታን መመልከት እና የእያንዳንዱን ሰብል የጤና ሁኔታ በጥልቀት መመርመር ስለሚችሉ ብለዋል -- ኪሩቤል መንበሩ አለሙ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።''ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የሳተላይት ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ቁጥጥርን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅን፣ ዝናብ እና5 የመሬት መራቆትን ስለመከታተል ኪሩቤል መንበሩ አለሙ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያይተናል።በክፍል ሁለት እንደ ብሪክሱ አዲስ የልማት ባንክ ያሉ ተቋማት የአፍሪካ ባንኮች ስርዓታቸውን በማዘመን በቂ አገልግሎት ላልተዳረሰባቸው ማኅበረሰቦች የፋይናንሺያል ተደራሽነትን ለማስፋት እንዴት እንደሚረዱ ፕላሲዲየስ ካስቱስ (ኢንጂነር) በታንዛኒያ የግል የንግድ ድርጅት ባለቤት ምልከታቸውን አጋርተውናል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

''ቻይናን፣ ሩሲያና ህንድ የመሳሰሉ ሀገራት የራሳቸውን አሻራ እያስቀመጡ ነው እየመጡ ያሉት፤ ጠንካራ የሚባል ኢኮኖሚ፣ ሰራዊት፣ ዲፕሎማሲ ገንብተዋል። በተለይ ከግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠሩ ነው — የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ ስርዓት ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተለወጠ እንደሆነ ማየት እንችላለን '' ሲሉ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ፕሮግራማችን የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የዓለም ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓትና የወደፊት ዕጣን በተመለከተ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ጋር እንቃኛለን። በክፍል ሁለት የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አገራዊ ፖሊሲዎችን ከአህጉሪቱ የጋራ ፍላጎቶች ጋር የማጣጣም አስፈላጊነትን በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ለሚ ጋር እንዳስሰዋለን።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

'' በምዕራቡ በኩል የሚነገረው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ እረዳለሁ። አብዛኛው የሚነገረው እውነት የሆነ፣ መሬት ያለው ነገር አይደለም። ዛሬም ያ ነገር ቀጥሏል። ይሻሻላል ተብሎ ቢጠበቅም ያው ነው አሁንም — ያንን ሀገር ፈርጆ ላይ ላዩን ሊጭኑብህ የሚፈልጉት ነገር አለ '' ሲሉ የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪ ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሱበበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ ሩሲያ በአፍሪካዊያን ዓይን እንዴት እንደምትታይ መሰረት በማድረግ የቀደመ የሚዲያ ትርክቶችን መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር በማነፃፀር የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪ ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በኢራን ጦርነት ሳቢያ ከተፈጠረው የኃይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ እንደ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ አፍሪካዊ ፕሮጀክቶች ችግሮችን ለመቋቋም የሚኖራቸውን ፋይዳ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ዳይረክተር ሞገስ መኮንን ጋር ዳሰነዋል፡፡ ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

''ያሉንን የተፈጥሮ ኃብቶች በአግባቡ እየተጠቀምን አይደለም። የግብርና መሠረተ ልማት ከፍተኛ ምርት ለማውጣት እንደ ጀርባ አጥንት የሚወሰድ ነው — መንግስታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ቢታወቅም ከውጪ የሚሸመቱ ምግቦችን ለመቀነስ አሁንም ብዙ ነገሮች ይጠበቅባቸዋል '' ሲሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል።ሁለት ጉዳዮች በሚቃኙበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ከፍተኛ የተፈጥሮ ኃብት ያላት አፍሪካ ስለምን በከፍተኛ ሁኔታ ከውጪ ተሸምተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምግቦች ጥገኛ ሆነች ደግምስ ቀጣዩ ዘመናት ምን መምሰል አለባቸው ስንል በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በአፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት። ከስኬቷ ጀርባ ያለውን ምስጢር እና ሌሎች ሀገራት ሊውስዱ የሚችሉ ተሞክሮዎችን ምሪሺየሳዊ የምህንድስና እና የከተማ ቄየሳ ባለሙያው ቪነሽ ቺንታራም አስረድተውናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

''ዋሽንግተን መሪዎችን በመግደል እና ኃይሏን በመጠቀም ኢራንን በአጭር ግዜ ውስጥ አንበረክካለሁ ብላ አስባ ነበር። በተቃራኒው ኢራን ድብደባዎቹን ተቋቁማ፤ መከላከሏን ቀጠለች እንዲሁም የጦር ሜዳውን ወደ ባሕረ ሰላጤው፣ ወደ አረቦች እና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፋፍታለች። በዚህም አሜሪካ የበላይነቷን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች ”- የወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ስለመሆኑ ከጂዮፖለቲካዊ አኳያ ከወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል በአፍሪካ ያለውን የጸጥታ እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃገብነት ጉዳይ ከሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰር ጋር ቃኝተነዋል። በመጨረሻው ክፍል ከሚያዝያ 8-9 ፣ 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው የአደጋ ስጋት አስተዳደር አቅምን በተመለከተ ከቻርሎት ኖርማን፣ የጋና ብሔራዊ የአደጋ አስተዳደር ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር ጋር ዳሰነዋል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ዓለም የባዮሎጂካል ብዝሃነት ዓለም አቀፍ ቀንን በፈረንጆቹ ግንቦት 22 ቀን ያከብራል።'' አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የተጋለጠች አህጉር ነች፣ በእርግጥ አንድ ዓይንት ስነ ምህዳር አይደለም ያላት። ስለዚህ ይህ የሀገር በቀል እውቀት ለብዝሃ ህይወት ይጠቅማል። ብዝሃ ህይወት ስንል ብዙ ዝርያ ያላቸው እንስሳት፣ ዕፅዋትና ደቂቀ ነፍሳትን አንድ ላይ የያዘ ነው '' - ሲሉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካን ስነ ኑረቶችና ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን ሚናዎች የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ጋር ቆይታን አድርገናል። በክፍል ሁለት አፍሪካ በዓለም አቀፍ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ዕድገት ጉዞ ያላትን ቦታ ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሰርቨር ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሙያው ታደሰ ፀሃይነህ ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

''ራሺያኖች ሉዓላዊነታቸውን በመጠበቅ፣ ራሳቸውን በማስታጠቅ እና በአርበኝነት ረገድ በጣም ጥሩ ናቸው። ባህላቸውም በሚገባ የጎለበተ እና የተብላላ ነው። ስለዚህ አፍሪካዊያን ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት የቅኝ ግዛት ግንኙነት ከሌላት ራሺያ ብዙ መማር ይችላሉ '' ሲሉ የእዮብዘር ዘውዴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝቀት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የራሺያ 81ኛው የድል ቀንን መሠረት በማድረግ ከፓን አፍሪካኒዝም አንድነት ጋር በማስተሳሰር የዮብዘር ዘውዴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ጋር በስፋት እንወያያለን። በክፍል ሁለት ከፈረንጆቹ ግንቦት 7 - 8፣ 2026 በአዲስ አበባ ስለተከናወነው የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔን በተመለከተ እውቁ ጋናዊ ዩቱበር ዎዴ ማያ ሀሳቡን ያካፍለናል። ሙሉውን መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

''አሁን ላይ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አስፈሪ በሚባል ደረጃ እየሄደ ያለ ነው። የተለያዩ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው። እነዚህ ልጆችም ለማይሆኑ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ — የዲጂታሉ ዓለም ገደብ የለውም። ከስነልቦና፣ ከእውቀታቸውና ራሳቸውን መቆጣጠር ከሚችሉበት በላይ የሆኑ ነገሮችን እየተመለከቱ ለብዙ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ። ጥፋቱ ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን - '' ሲል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋራው ብሩክ ጫላ ለስፑትኒክ አፍሪካ አፍሪካ ተናግሯል ።ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ዝግጅቱ በክፍል አንድ ታዳጊ አፍሪካውያን ህጻናትን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ካልተፈለጉ ጫናዎች ስለመከላከል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋረው ብሩክ ጫላ ዕይታውን ያጋራናል። ክፍል ሁለት እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ እና የዓለም ባንክ ባሉ ተቋማት በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ደረጄ መለስ ጋር እንወያያለን። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

''መሪዎችን መግደል፣ ዜጎችን መግደል፣ ሁሉም ነገር እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ግፍ ነው። እኛ የምንላችሁን ስሙ፣ እኛ ኃያላን ነን፣ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን ነው የሚሉት። ኢራን በቀጥታ የተፈፀመባት ወረራ ነው -'' ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አሌክሳንደር ኃይማኖት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በክፍል አንድ ሰሞነኛው የኢራን - አሜሪካ - እስራኤል ግጭትን መሠረት አድርገን በህገወጥ መንገድ በተለይም በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ስለሚደረጉ የመንግስት ለውጥ ከሀገራት ሉዓላዊነት እና ህጋዊ አንድምታዎች አኳያ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አሌክሳንደር ኃይማኖት ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ከሩሲያ - ኢትዮጵያ ንግድ ፎረም መነሻነት በሀገራቱ መካከል ያለ የሁለትዮሽ ንግድ ግንኙነትን ከዋሲሁን ፍቅሬ የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሮዝዳነት ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር ዳሰናል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: